Ethiopian Electric Utility
History of Nekemte
Posted by admin on 2024-01-18 18:30:00 |
Last Updated by jeeu on 2026-03-18 10:03:31
Share: Facebook |
Twitter |
Whatsapp |
Telegram Visits: 102
ተቋማችን በዲስትረቡሽን መስመሮች እርጅና ምክንያት በከተሞች አካባቢ የሚስተዋለውን የኃይል መቆራረጥና መዋዥቅ ችግር በዘላቂነት ለመፍታት መጠነ ሰፊ የዲስትሪቡሽን መስመሮች መልሶ ግንባታና አቅም ማሳደግ ስራዎች እያከናወነ ይገኛል፡፡
ከእነዚህም መካከል በወላይታ ሶዶ፣ በሐረር፣ በሻሸመኔ፣ በደብረማርቆስ፣ በጎንደር እና በኮምቦልቻ ከተሞች እየተከናወነ የሚገኘው የ6ቱ ከተሞች መልሶ ግንባታና አቅም ማሳደግ ፕሮጀክት 87 በመቶ ተጠናቋል፡፡
በሐረር ከተማ 28 ኪ.ሜ የመካከለኛ እና 40.75 ኪ.ሜ የዝቅተኛ መስመር ተዘርግቷል፤ 3 ሺህ 549 የመካከለኛ እና የዝቅተኛ መስመር ተሸካሚ የኮንክሪት ምሰሶዎች ተተክለዋል፡፡
በወላይታ ሶዶ ከተማ 79.20 ኪ.ሜ የመካከለኛ እና 80.66 ኪ.ሜ የዝቅተኛ መስመር ተዘርግቷል፤ 4 ሺህ 772 የኮንክሪት ምሰሶዎች ተከላ ተከናውኗል፡፡
በፕሮጀክቱ በሻሸመኔ ከተማ 5 ሺህ 666 የኮንክሪት ምሰሶዎች በመትከል 76 ኪ.ሜ የመካከለኛ እና 46.17 ኪ.ሜ የዝቅተኛ መስመር ለመዘርጋት ተችሏል፡፡
በተመሳሳይ በደብረማርቆስ ከተማ 3 ሺህ 550 የኮንክሪት ምሰሶዎችን በመትከል 28.52 ኪ.ሜ የመካከለኛ መስመር የተዘረጋ ቢሆንም የዝቅተኛ መስመር ስራ አልተጀመረም፡፡
እንዲሁም በጎንደር ከተማ ለፕሮጀክቱ ከሚያስፈልገው አጠቃላይ 6 ሺህ 278 ምሰሶዎች ውስጥ 5 ሺህ 095 ምሰሶዎች ተተክለዋል፤በዚህም 65 ኪ.ሜ የመካከለኛ እና 29.45 ኪ.ሜ የዝቅተኛ መስመር ተዘርግቷል፡፡
በአንፃሩ በኮምቦልቻ ከተማ የመካከለኛ እና የዝቅተኛ መስመር ዝርጋታ ያልተጀመረ ቢሆንም፤ 190 የመካከለኛና የዝቅተኛ መስመር ተሸካሚ የኮንክሪት ምሰሶዎች ተተክለዋል፡፡
ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ ከከተሞቹ እድገት ጋር ተያይዞ ይስተዋል የነበረውን የኃይል መቆራረጥና መዋዥቅ ችግር በዘላቂነት ይፈታል ተብሎ ይታመናል፡፡